የኢትዮጵያ ባሃኢዎች ብሔራዊ መንፈሳዊ ጉባኤ
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • መልእክት ይላኩልን
    • ለበለጠ መረጃ

አልኮልና አደንዛዥ ዕፆች መከልከል


ለበሽታ ፈውስ ካልሆነ በስተቀር የአልኮል መጠጥንና በአደንዛዥ ዕፆች መጠቀምን ባሃኦላህ ፈጽሞ አውግዞታል።

መደሰትና መዝናናት
የባሃኢ ትምህርት የተመሠረተው ለማንኛውም ነገር በመጠነኛነት እንጂ በብሕትውና አይደለም። መልካምና ውብ በሆኑ መንፈሳዊና ቁሳዊ ነገሮች መደሰት የተደገፈ ብቻ ሳይሆን የታዘዘም ነው። ባሃኦላህ “ለእናንተ ሲባል በተፈጠሩ ነገሮች ከመጠቀም አትታገዱ” ይላል።

ደግሞም እንዲህ ይላል፦
“ፊታችሁ በደስታና በከፍተኛ ክብር ያንጸባርቅ ዘንድ ይገባዋል።”

አብዱል-ባሃ እንዲህ ይላል፦
“የተፈጠረው ሁሉ ለፍጥረታት ቁንጮ ለሆነው ለሰው ልጅ ሲሆን፥ እሱም ለዚህ መለኮታዊ ስጦታዎች ማመስገን አለበት። ማንኛውም ቁሳዊ ነገር ሁሉ ለእኛ አገልግሎት ነው። ለዚህም በማመስገናችን፥ ሕይወት መለኮታዊ ስጦታ መሆኑን ለመረዳት እንችላለን። ሥጋና መንፈሳዊ ኑሮአችን የመለኮታዊ ትምህርት መገለጫ በመሆናቸው ሕይወትን ከጠላን ምስጋና ቢሶች መሆናችን ነው። ስለዚህ በመደሰትና ሁሉንም ነገር በማድነቅ ጊዜያችንን በምስጋና ማሳለፍ አለብን። ” (ዲቫይን ፎሎሶፊ ገጽ 104)

በባሃኢ ሃይማኖት የቁማር ጨዋታ መወገዝ ማናቸውንም ጨዋታ ያጠቃልል እንደሆነ አብዱል-ባሃ ተጠይቆ እንዲህ ብሏል፦
“አይደለም፤ አንዳንድ ጨዋታዎች ተንኮል የለባቸውም። በተለይም ጊዜን ለማሳለፍ ከተደረጉ ጎጅነት የላቸውም። የሆነ ሆኖ ጊዜ ለማሳለፍ መሞከር የጊዜ ማባከን ጥፋት ያስከትል ይሆናል። በእግዚአብሔር እምነት ጊዜን ማባከን ተገቢ አይደለም። ነገር ግን አካላዊ ኃይል ለማጎልመስና ለማጠንከር የሚደረጉ ልምምዶች አስፈላጊ ናቸው።” (ኤ ሄቮንሊ ቪስታ ገጽ 9)

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

ህግጋት

  • ሥራ ስግደት ነው
  • በዓላትን ማክበር
  • ባሃኢ ምንድን ነው?
  • አልኮልና አደንዛዥ ዕፆች መከልከል
  • ጋብቻ
  • ፀሎት
  • ፆም
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2021 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች ብሔራዊ መንፈሳዊ ጉባኤ

Go Top